Who We Are

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ ሥራ ፈላጊዎችን የመመዝገብ ፣ የማደራጀት ፣ ወደ ሥራ የማስገባት ፣ ኢንተርፕራይዞችን የመደገፍ ፣ የገበያ ትስስርና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ የማመቻቸት ፣ ሥራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ፍቃድ መስጠትና የመቆጣጠር ፣ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት የሚፈልጉ ዜጎችን የማሰልጠን ፣ የውጭ አገር ሥራ ሰምሪት ኤጀንሲዎችን የመቆጣጠርና ህግና ሥርዓት አክብረው እንዲሰሩ የማድረግ ተግባራትን ያከናውናል።

አመሰራረት
ታሪካዊ ዳራ
1+
sebols
1+
sebols
1+
sebols
1+
sebols

ራዕይ እና ተልዕኮ

ራዕይ፡ ብቁ የሰው ሀብት፣ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል የሞላባት ኢትዮጵያን ማየት ነው ።
ተልዕኮ፡ ገበያ-መር የክህሎት ልማትን እውን በማድረግ፣ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚ ማድረግ ነው ።

ስትራቴጂክ ዓላማዎች

ጥቅል ዓላማ፡ በሥራ ገበያ ፍላጎት መሠረት ክህሎቱ የዳበረ የሰው ኃይል በማፍራት፣ ምቹ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት በማስፈን የዜጎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ።
ዝርዝር ዓላማዎች፡
በሥራ ገበያ ፍላጎት መሠረት ብቁና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ የሚያሸጋግር የሥራ ኃይል ማፍራት ።
ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠርና በማስፋፋት የዜጎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ።
ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነትን ማስፈን ።

የቢሮው እሴቶች

ብቁ መሆን
መብትና ግዴታውን የለየ
ችግር ፈቺ
የተሟላ ስብዕና ያለው
ብርቱ እና ተባባሪ

ስትራቴጂክ ግቦች

ግብ 1፡ ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም፣ የሀብት አጠቃቀም እና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራርን ማጎልበት
ግብ 2፡ የሥልጠና እና የኢንተርፕርነርሺፕ ክህሎት ልማት አግባብነት፣ ጥራትና ተደራሽነት ማረጋገጥ
ግብ 3፡ ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎች ተጠቃሚነትን ማሳደግ.
ግብ 4፡ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሚና ማሳደግ
ግብ 5፡ የኢንዱስትሪ ሰላምና የሥራ ላይ ደህንነት ማረጋገጥ.