የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በተገኙበት “ደቡብ ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ቃል በአርባ ምንጭ ከተማ የተዘጋጀው ባዛርና ኤግዚቪሽን በይፋ ተከፍቷል።
በባዛርና ኤግዚቪሽኑ ላይ በክልሉ የሚገኙ ከ70 በላይ አምራች እንዱስትሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ምርቶቻቸውን እንደሚያስተዋዉቁ ይጠበቃል።
መርሃ ግብሩ በክልሉ የሚገኘውን እምቅ የአምራች ኢኔዱስትሪ ዘርፍን ከማስተዋወቅ አንፃር የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ተገልጿል።
ባዛርና ኤግዚቪሽኑ ምርቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ እና የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ምቹ መደላድል እንደሚፈጥርላቸውም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።
መርሃ ግብሩን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚንስትር ድኤታ አቶ ታረቀኝ ቡቡልታ ጨምሮ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞንን ፣ የክልል፣ የጋሞ ዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የተገኙ ሲሆን ባዛርና ኤግዚቪሽኑ ለ4 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል።

