የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ከዓለም አቀፍ ሥራወች ድርጅት/ILO/ ጋር በመተባበር በክልሉ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳና ከተማ እንዲሁም በወናጎ ወረዳ በቡና ሥራ ላይ የተሰማሩ የሕብረት ሥራ ማህበራትና የግል ድርጅቶች የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ የድጋፍና ክትትል ስራ አድርገዋል።
ድጋፍና ክትትሉ በቀጣይ ማህበራትና የግል ድርጅቶች የቡና ምርትን እሴይ ሰንሰለት መሠረት ባደረገ መልኩ የሥራ ቦታወችን ለማሻሻል/ምቹ ሥራዬ/ በሚል ፕሮጀክት ወደ ተግባር ለመግባት ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።
አቶ ግርማ ሙሉጌታ የቢሮ አሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ ተወካይ ለማህበራቱ በቡና እሴይ ሰንሰለት አተገባበርና በቡና ምርት አዘገጃጀት እንዲሁም በሠራተኞች አሰተዳደራዊ አያያዝና የሚፈጸሙ ተግባራት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል።
አቶ ግርማ ሙሉጌታ በገለጻ ወቅት እንደተናገሩት በየትኛውም ማህበራትና በግል ድርጅት የሚሰማሩ ግዜአዊና ቋሚ ሠራተኞች በሥራና ክህሎት ቢሮ በኩል እውቅና አግኝተው መሠማራት እንዳለባቸው ገልፀው ከዚህ ውጪ እንዳይሆን ባለድርሻ አካላት የበኩሉን መወጣት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የሚተገበረዉ እያንዳንዱ የኢንዱስትሪ ተግባራት ዘመን ቀማሽ እና በቴክኖሎጅ የታገዘ እንድሆን ድጋፍና ክትትል ለተደረገላቸው በቡና ምርት ዝግጅት ለተሠማሩ ማህበራትና ለግል ድርጅቶች ሰፍ ገለፃ ተሰጥቷል።
የዓለም ሥራዎች ድርጅት ተወካዮች የፕሮጀክቱን ዋና ዓላማ አስመልክተዉ እንደገለፁት በኢንዱስትሪዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን አይተው ወደፊት ችግር ፈች ጥናት ለማድረግና ውጤት ለማምጣት በቡና እሴይ ሰንሰለት ላይ ለተደራጁ ማህበራትና ለግል አሠራና ሠራተኛ ድርጅት በቡና ምርት ጥራት ዝግጅት እንድሁም በሠራተኞች አስተዳደራዊ ተግባር እና በህፃናቶች ጉልበት ብዝበዛ ላይ አስፈላጊ ጥናታዊ መረጃ በመውሰድ በቀጣይ መሠራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተዉ ለመሥራት እንደሆነ አብራርተዋል።
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር የሞፕላኮ/Moplaco/ ኋ/የተ/የግ/ማህበር ተወካይ አቶ ሽመልስ ሀይሉ እንደገለጹት ድርጅቱ እየሠራ ያለው የእስፐሻሊቲ ቡና ምርት አዘገጃጀት ላይ ስሆን ከሚያቀርባቸው ቡና ምርት አንጻር የዓለም አቀፍ ተወዳዳርዎች እንደሆኑና ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት ለአለም ገበያ እንደሚያቀርቡ አስረድተዋል።
የክልሉ ቡናና ሻይ ቅመማቅመም ባለሥልጣን፣የጌዴኦ ዞን ቡናና ሻይ ቅመማቅመም ዘርፍ ኃላፊ፣ የዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ አሰሪና ሰራተኛ የሁለቱ ዳይሬክተር አስተባባሪዎች እንዲሁም ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የባለድርሻ አካላት በድጋፍና ክትትሉ ስራ ታሳታፊ ሆነዋል።
ዘገባዉ የቢሮዉ ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ዳይረረክቶሬት ነዉ።
