የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪትና ገበያ ልማት ዘርፍ በክልሉ በ4 ዞኖች ዉስጥ በሚገኙ በ12 ወረዳዎች ሥር ባሉ 76 ኢንተርፕራይዞች ላይ በ36 የገጠር ቀበሌያት የሥራ ማዕከላትን ማስከፈት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት አካሂዷል።
አቶ ዘዉዱ ሳሙኤል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሥራ ስምሪትና ገበያ ልማት ዘርፍ ኃላፊ በዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች የተጠናዉን የመጀመሪያዉን ዙር የጥናት ዉጤት ሪፖርት ገምግመዋል።
የገጠር ሥራ ማዕከላትን ለማስከፈት የሚያስችል ዝርዝር የዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በምክትል ርዕሰ መስተዳድርና በቢሮ ኃላፊ በዶክተር አበባየሁ ታደሰ አቅጣጫ መቀመጡን የጠቆሙት አቶ ዘዉዱ በከተሞች ወደ 192 የሥራ ማዕከላት መኖራቸዉን ጠቁመዉ በገጠር የሥራ ማዕከላትን ለማስከፈት የዳሰሳ ጥናት ማስፈለጉን ተናግረዋል።
አቶ ዙዉዱ አክለዉ የዳሰሳ ጥናቱ በገጠር የሥራ ማዕከላትን ለማስከፈት በእጃችን ምን ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ በጥናቱ ተለይቶ መታወቅ እንደሚገባ የጠቆሙት ሲሆን መሠረ-ተልማት ሁኔታ ፣ ለድጅታል ቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነ የሰዉ ኃይል እንዲሁም የኤሌክትሪክ ሲስተም የመሳሰሉት በጥናቱ መካተት የሚገቡ ጉዳዮች ተካቶ በቀጣይ ዳብሮ ለቢሮ ማኔጅመንት እንዲቀርብ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በጥናቱ የክልሉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ጨምሮ የዞንና የወረዳ መዋቅር ማኔጅመንት አካላት እንዲሁም የቀበሌ የሥራ ዕድል ፈጠራ ግብረ-ሀይል ታሳታፊ ሆነዋል።
ዘገባዉ የቢሮ ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነዉ።